Under Construction
This will close in 20 seconds
የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ሠራተኞች ማኅበር መጀመሪያ ጥር 8 ቀን 1958 ዓ.ም ተመሠረተ፡፡ እንዲሁም መጋቢት 17 ቀን 1968 ዓ.ም. እንደገና ተደራጅቶ እና ተጠናክሮ ተመስርቷል፡፡ ማህበሩ የሰራተኛውን የስራ ዋስትና እና ደህንነት ለማስጠበቅ፤ ሰራተኛው ምርታማነትን በማሳደግ ከተቋሙ የተሻለ የጥቅም ተጋሪ የሚሆንበትን አቅጣጫ ከማኔጅመንት ጋር በመነጋገር ማስቀመጥ፤ የተቋሙን ራዕይ ፤ ተልዕኮና ዓላማን ለማሳካት ከማኔጅመንት እንዲሁም ከሰራተኛው ጋር በየጊዜው በመመካከር የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ የራሱን አስተዋፅኦ ማድረግ፤ የሰራተኛውን ጥቅማጥቅም ለማስከበርና ከቀደመው የተሻለ መብትና ጥቅም ለማስገኘት በየጊዜው በሁለትዮሽ ላይ የተመሰረተ የህብረት ስምምነት ከማኔጅመንት ጋር በመደራደር እንዲሁም በትክክል ለመፈጸሙ በየደረጃው ክትትል በማድረግ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፍላጎታቸው የተሟላ ሰራተኞች እንዲኖሩ ማስቻል፤ እና ሌሎችንም አላማዎች ለማሳካት ይህ ማህበር ተመስርቷል፡፡በዚሁ መሰረት አሁን ላይ ከአስራ ሶስት ሺ በላይ አባላት በማህበራችን በመታቀፍ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ከማህበራቸው በማግኘት ላይ ይገኛሉ፡፡
ውድ የማህበራችን አባላት በአለም አቀፍ ደረጃ ማህበራት ሲቋቋሙ የተለያየ አላማን አንግበው መሆኑ ይታወቃል፡፡ የሰራተኛ ማሕበር ደግሞ ከእነዚህ ማህበራት ውስጥ ሲሆን አጠቃላይ አላማውን የሰራተኛውን የስራ ዋስትና ፤ መብቶች እና ጥቅሞችን ማስከበር ብቻ ላይ ሳይወስን አዳዲስ ጥቅማጥቅሞችንም በማስገኘት ሰራተኛውም በምላሹ ለተቋሙ ያለውን ዕውቀት እና ጉልበት በሙሉ ሳይሰስት እንዲሰጥ እና ከፍተኛ የሆነ የባለቤትነት መንፈሥ እንዲያደረጅ ያግዘዋል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም መሰረታዊ ሰራተኞች ማህበር ያለፉትን አርባ አመታት በብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ በማለፍ ዛሬ ላይ ደርሷል ፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገው ጥረት በየጊዜው እየጨመረ የመጣ ሲሆን ለዚህም የአባላቱ ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ምስጋና እያቀረብን በቀጣይም ይህንን የጋራ ሃላፊነት የመወጣት ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ እንጠይቃለን፡፡ በዚህ የማህበራዊ ኃላፊነት ማህበራችን የህብረተሰቡን የልማት ተግባር ለመደገፍ፣ የማህበረሰብ ቀውስ ሲፈጠር፣ በችግርና በተመሳሳይ ክስተቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚያከናውነው ተግባር ነው፡፡
የመኖሪያ ቤት ችግር ከመቅረፍ አንጻር ማህበራችን እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ደካማ ነው ስለዚህ በቀጣይ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር መፍትሄ ብትፈልጉልን እንላለን፡፡
የላፕቶፕ ግዢ ጥያቄ ብናቀርብም ማህበሩ እስካሁን ጥያቄያችንን ሊመልስልን ባለመቻሉ አዝነናል፡፡
የሁለተኛ ዲግሪ ለመማር እድችል በማህበሬ በኩል የተደረገልኝ ድጋፍ ህልሜን እንዳሳካ አድረጎኛል በተጨማሪም በተቋሙ ውስጥ የሚኖረኝ የስራ ድርሻ በማሳዳግ ድርጅቴን የተሻለ ማገዝ ችያለሁ፡፡ በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡
ከዚህ ቀደም ከተቋሙ ጋር በነበረኝ አለመግባባት ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ቢያመራም የሰራተኛ ማህበሩ ያደረገልኝ የህግ ምክር እንዲሁም የተቋረጠውን ደሞዜ በመክፈል ድጋፍ ያደረገልኝ ሲሆን ጉዳዩን ጠነቃ ቀጥሮ በመከራከር ልረታ አስችሎኛል፡፡
ማህበራችን ለውጭ ህክምና ድጋፍ እነደሚሰጥ አላውቅም ነበር፡፡ የስራ ባልደረባችን ለከፍተኛ ህመም በመዳረጉ ምክኒያት ወደውጭ ሄዶ እንዲታከም የሜዲካል ቦርድ መወሰኑን ተከትሎ ሰራተኞች ድጋፍ እንዲያደርጉለት ለማስተባበር በማህበር ቢሮ በተገኘሁበት ወቅት በተሰጠን መረጃ ነው ላውቅ የቻልኩት፡፡ በእውነቱ በወቅቱ የተሳማንን እፎይታ ከምገልጸው በላይ ነው፡፡ እናመሰግናለን፡፡
በማህበሩ በኩል በተደረገልን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዢ በጣም ደስተኞች ስንሆን አሁን በቤታችን ሆነን በስማርት ቲቪያችን አማካኝነት በመረጃና በመዝናኛ ፕሮግራሞች እየተዝናናን ሲሆን ከፍሪጁም የቀዘቀዘውን በማውጣት በስቶቫችን እያሞቅን እየተመገብን ልብሶቻችንንም ያለምንም ድካም በማጠቢያ ማሽን በመታገዝ እያጠብን የስራ ቀናችን በጉጉት እንጠብቃል፡፡ ለማህበራችን ችርስ በሉልን፡፡
በአካባቢያችን ባለው የውሃ ችግር ምክኒያት ብዙ ጊዜ ውሀ እየገዛሁ ነበር የምጠቀመው አሁን በቀረበው የውሃ ማጣሪያ አማካኝነት ስንፈልግ የሞቀ ካለሆነ የቀዘቀዘውን በመቅዳት ቤተሰቦቼ ያለምንም ችግር እየተጠቀምን እንገኛለን፡፡ ግልግል፡፡ ማህበራችን ዘምኖ አዘመነን……
የማህበሩ አባላት መብት፤ ጥቅምና ደህንነት በማስከበር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎታቸው እንዲሟላ ምርታማነታቸው እንዲጎለብትና ሰራተኞች ፍትሀዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ የድርጅታችንን ተልዕኮ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሳካ በማገዝ በሀገሪቱ ግንባር ቀደም ማህበር መሆን ነው፡፡