Under Construction
This will close in 20 seconds
የማህበሩ አባላት በህገ-ደንብ ከተቀመጡ ጥቅማ-ጥቅሞች ባሻገር ማህበሩ ባለው ተቀማጭ ገንዘብ የተለያዩ የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎችን በመግዛትና በበድር በማቅረብ አባላት በኢኮኖሚ የሚታገዙበት ማዕቀፍ ነው፡፡
የማህበሩ አባላት በስራቸው ወቅት በአሰሪው ለሚደርስባቸው ኢ-ፍትሃዊ እርምጃ ማህበሩ አግባብ አይደለም ብሎ ሲያምን እና የተቋሙን ህግና መመሪያ ተከትለው በሰሩት ስራ አግባብ ባልሆነ መልኩ በሚጠየቅበት ጊዜ የሚያገኙት የህግ አገልግሎት ነው፡፡
በማህበሩ ውስጥ ከአንድ ዓመት በላይ በአባልነት የቆዩ ሠራተኞች በግላቸው ሁለተኛ ዲግሪያቸውን (MASTERS DEGREE PROGRAM) ለመማር የሚያስችላቸውን የመግቢያ ፈተና አልፈው ትምህርት መጀመራቸውን የሚያሳይ መረጃ ለማህበሩ ካቀረቡ ከወለድ ነፃ ብድር ይሰጣቸዋል፡፡
በሕጋዊ መንገድ ክሊራንስ (CLERANCE) አቅርቦ መሥሪያ ቤቱን ለሚለቅ ሠራተኛ በአባልነት የቆየባቸውን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ ክፍያ ይከፈለዋል፡፡ ማንኛውም የማህበሩ አባል እድሜው ለጡረታ ደርሶ በሚገለልበት ጊዜ ጡረታ መውጣቱን ማስረጃ ሲያቀርብ በአባልነት የቆየባቸውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ክፍያ ይከፈለዋል፡፡
የማህበሩ አባል በአገልግሎት ላይ እያለ በማንኛውም ሁኔታ ቢታመም እና ሕመሙ ከፍተኛ ሆኖ ወደ ውጭ አገር የሚያስኬድ ከሆነ ድርጅቱ ከሚሰጠው በተጨማሪ ማህበሩ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል ።
አንድ የማህበሩ አባል ከዚህ ዓለም በሞት በሚለይበት ወቅት በማህበሩ ህገ ደንብ መሰረት ለማች ሕጋዊ ወራሾቹ ወይም ቤተሰቦቹ የቀብር ማስፈፀሚያ እና የአበባ ጉንጉን ማህበሩ ያቀርባል፡፡