የኢትዮ ቴሌኮም መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር በአዲስ አበባ ከሚገኙ የተለያዩ ዞኖች እንዲሁም በደቡብ ምሥራቅ ሪጅን/አዳማ/ ከሚገኙ የማህበሩ አባሎች ስለ ማህበሩ የሥራ እንቅስቃሴና የተቋሙ ቀጣይ ለውጦች ላይ ምክክር የተደረገ ሲሆን በመድረኩ ተነስተው ውይይት ከተደረገባቸው አንኳር ነጥቦች ውስጥ ማህበሩን በተመለከተ ስለ ማህበሩ ዓላማ፤ ከካርየር ፕሮግሬሽን ጋር ተያይዞ የተሰሩ ሥራዎች፤ ከባንክ ብድር ጋር በተያይዘ የተደረጉ እንቅስቃሴዎች፤ የዲስፕሊን ግድፈቶች በተመለከት፤ ከኮቪድ_19 ጋር ተያይዞ እየተሰሩ ያሉ የመከላከል ስራዎች፤ በህብረት ሥምምነቱ እንደአዲስ ስለተካተቱ የቆላ ቦታዎችና አበሎች፤ የቦነስ ክፍያና ደመወዝ ጭማሪ ጥያቄዎችን በተመለከተ፤ ለውጭ ህክምና ስለተደረጉ ድጋፎች፤ የሠራተኞች የመረዳጃ ዕድር አጠቃላይ ሁኔታን በተመለከተ፤ የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ አገልግሎት፤ ለማስተርስ ተማሪዎች የተደረገ የብድር ድጋፍ፤ አባላትን ተጠቃሚ ስለሚያደርገው የኤሌትሮኒክስ ግዢ፤ ማህበራዊና ሃገራዊ ሃላፊነትን ከመወጣት አንፃር በተደረጉ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ከተቋሙ ለውጥ (ሪፎርም) ጋር በተያያዘ ሰራተኞች ወደፊት ሊኖራቸው ከሚችሉ ተግባራት ውስጥ ተቋሙ ካስቀመጣቸው የስትራቴጂክ ግቦች ውስጥ ትኩረት ሰጥተው ሊመለከቷቸው ከሚገቡት ውስጥ የአሰራር ልህቀት በተመለከተ/ OPERATIONAL EXCELLENCE/፤ የፋይናንስ አቅምን ከማሳደግ አንጻር /FINANCIAL CAPACITY/፤ የድርጅቱን ደህንነት መጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታዎች /ORGANIZATIONAL SECURITY፤ የሃብት አስተዳደርና አጠቃቀምን በተመለከተ/RESOURCE MANAGEMENT & UTILIZATION/፤የአገልግሎት ጥራትና ተሞክሮዎች ምን እንደሚመስሉ/ QUALITY OF SERVICE & EXPERIENCE/፤ ድርጅታዊ ባህልና ምርታማነት ከማሳደግ/CORPORATE CULTURE & PRODCUCTIVITY/፤ በሚሉ ሰፊና ጥልቅ ርዕሶች ላይ ገለጻና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮም ይዞት የተነሳውን ራዕይ እንዲያሳካ በአንፃሩም የሰራተኞችን የስራ ዋስትና አደጋ ላይ የማይወድቅበት እና ሀገራችን በዘርፉ ማሳካት ስለምትፈልገውና በአጠቃላይ የሁሉንም ወገን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ለውጥ እንዲሆን ለማስቻል ማህበራችን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ውይይት ተደርጓል፡፡ ተቋማችንም የተለያዩ ስትራቴጂ እና ስትራክቸር በመስራት በገቢያው ውድድር ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን ጥረት እያደረገ ይገኛል ፡፡ አጠቃላይ ለውጡን ተከትሎ ሊመጣ የሚችሉ ነገሮችን ቀድሞ በመረዳት ስልጠና ለአመራሮቹ በማሰጠት ዝግጅት ማድረግ የሚቻልበትና ሰራተኛው በርትቶ ከለውጡ ጋር አብሮ ለመሄድ የሚችልበትን አካሄድ ለመቅረፅ ተሞክሯል፡፡ ከማብራሪያውም በኋላ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎች በአቶ ካሳሁን ሰቦቃ አማካኝነት በቂ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ተሰብሳቢውም ከስብሰባው ጥሩ ግንዛቤ እንዳግኘና በቀጣይም መሰል መድረኮችና የመረጃዎች መለወዋጦች ሊኖሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡