Under Construction

This will close in 20 seconds

የኢትዮ ቴሌኮም መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በደረሰው ጉዳት ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችንና ለመከላከያ ሠራዊታችን የ3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

ማህበሩ ለመከላከያ ሠራዊታችን የ1.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በጥሬ ገንዝብ በመከላከያ ዋና መ/ቤት በመገኘት በማህበሩ ሊ/መንበር አቶ ካሳሁን ሰቦቃ አማካኝነት ድጋፉን ያደረገ ሲሆን በጦርነቱ ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኞች በመጠለያ ካምፕ በመገኘት በዓይነት የ1.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ ይህንንም ድጋፍ አስመልክቶ ወደስፍራው ለሚጓዘው የማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ አባላት የሽኝት ፕሮገራም በዋናው መ/ቤት የተደረገ ሲሆን በፕሮገራሙ ላይም የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የዘርፍ አመራር አባላት እንዲሁም ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡ በዚህም ወቅትም ማህበሩ ያደረገውን ድጋፍና በጦርነቱ ምክኒያት በሃገራችን ላይ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ በስፍራው ለተገኙ አካላት የማህበሩ ሊ/መንበር አቶ ካሳሁን ሰቦቃ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ድጋፉን ለተረጂዎቹ ለማድረስ ለሚጓዘው ቡድን ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ማህበሩ  በአይነት የሰጠውን ድጋፍ ማለትም ፍራሽ፣ሩዝ፣ዘይት፣ፈሳሽ ሳሙና፣ዳይፐር፣የአጥሚት እህል፣ጁስና የህጻናት አልሚ ምግብ ተፈናቃዮቹ በሚገኙበት በደብረ ብርሃንና በሰመራ (ጭፍራ) በመገኘት ድጋፉ እንዲደርሳቸው አድርጓል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በደብረ ብርሃን ከተማ  በጦርነቱ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን የሰራዊቱን አባላት ሆስፒታል ድረስ በመገኘት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በሆስፒታሉ ሃላፊም ስለተጎጂ የሠራዊቱ አባላት ስለሚደረግላቸው እንክብካቢና ዕርዳታ ገለጻ የተደረገለት ሲሆን ማህበሩ በቀጣይም ጊዜ ተመሳሳይ ድጋፎችን እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል፡፡

Post a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Under Construction

This will close in 20 seconds