Under Construction

This will close in 20 seconds

የኢትዮ ቴሌኮም መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር አንደኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን በደቡብ ምስራቅ ሪጅን አዳማ ከተማ ከሰኔ 6-8 ቀን 2011 ዓ.ም አድርጓል፡፡ በስብሰባው ከሁሉም ዞንና ሪጅን የመጡ የምክር ቤት አባላት የተገኙ ሲሆን በመጀመሪያ ቀን ውሎው በማህበሩ ሊቀ መንበር አቶ ካሳሁን ሰቦቃ የቀረበውን የስራ አስፈፃሚ የስራ ሪፖርት አድምጦ በሪፖረቱ ላይ ያለውን አስተያየት አቅርቦ፤ ተወያይቶ የዕለቱን መርሃ-ግብር አጠናቀዋል፡፡ ምክር ቤቱ በሁለተኛው ቀን ስብሰባው ከአባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ከስራ አስፈፃሚ አባላት ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በመጨረሻ በቀጣይ የስራ ሁኔታ ላይ አቅጣጫ አሰቀምጠው ስበሰባው ተጠናቋል፡፡

በስብሰባው ማጠናቀቂያ ላይ ከተገኙት የማኔጅመንት አካላት መካከል  የሰው ሃይል ቺፍ ኦፊሰር አቶ አይተንፍሱ ወርቁ ማህበሩ ለተቋሙ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ቀላል የማይባል እንደሆነና ይህም በተቋሙና በሰራተኞች መካከል ያለው ግንኙነት ጤናማና ውጤታማ እንዲሆን ያስቻለ መሆኑን አንስተው ማኔጅመንቱ ለሰራተኞች የሥራ አፈፃፀም ሊያግዝ የሚችሉ በርካታ ማዕቀፎች እንደሚያጠናና ለተፈፃሚነቱ የበኩል ሁሉ እንደሚያደርግ በመግለፅ በቅረቡ ለሰራተኞች ለቤትና ለመኪና ግዢ የሚሆን የብድር ስምምነት ከተለያዩ ባንኮች ተስማምቶ እንደጨረሰና በቅርቡም ተፈፃሚ እንደሚሆን ለምክር ቤቱ ተሰብሳቢዎች የገለፁ ሲሆን በቀጣይም ከማህበሩ ለሚነሱ መሰል ሃሳቦች የማኔጅመንት አካላት ድጋፍ የማይለይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በመጨረሻም አባላቱ በስብሰባው ወቅት ከደቡብ ሪጅን የዘርፍ ሰራተኛ ማህበር በቀረበ ጥያቄ መሰረት ለአንድ የሪጅኑ ሰራተኛ ለሆነ የኩላሊት ታማሚ በተሳታፊዎች ከ27 ሺህ ብር በላይ ዕርዳታ እንዲሰበሰብለት ተደርጎ በባንክ አካውንቱ ገቢ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም በደቡብ ምስራቅ ሪጅን አስተባባሪነት በሪጅኑ ጽ/ቤት ዋና ዕቃ ግምጃ ቤት አካባቢ የጽዳት ዘመቻና የችግኝ ተከላ አካሂደው አባላቱ ወደመጡበት ዞንና ሪጅን ተመልሰዋል፡፡         

Post a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Under Construction

This will close in 20 seconds