የኢትዮ ቴሌኮም መሰረታዊ ሰራተኞች ማህበርበሰው ኃይል ዋና ክፍል ከኦርጋናይዜሽናል ዴቨሎፕመንት መምሪያ ጋር በትብብር ለ161 የማኅበሩ የሥራ አስፈፃሚና የዘርፍ አመራሮች የአመራር ክህሎት ማሳደጊያ/Leadership skill development ስልጠና በ6 ዙሮች የ3 ቀናት ስልጠና ተሰጠ፡፡ እንዲሁም ለ145 የማህበሩ ስራ አስፈፃሚና የዘርፍ አመራሮች የ5 ቀናት የድርድር እና አማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች/Negotiation and Alternative Dispute Resolution ስልጠና በ 6 ዙሮች እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡

ይህ ስልጠና ማኅበሩን በእውቀትና በብቃት መምራት የሚችል አመራር ለማፍራት እንዲሁም ከማኔጅመንት ጋር ለሚደረጉ ውይይቶችና ድርድሮች የተሻለ አቅም እንዲኖር የሚያስችል ሲሆን ከሰራተኛውም ጋር ለሚኖር የስራ ግንኙነትና የሠራተኛውን ጥያቄ በአግባቡ በመረዳት መልስ ለመስጠት የሚረዳ አቅም በመገንባት ረገድ የራሱ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎችም እንደነዚህ ዓይነት ስልጠናዎች ከማህበሩ ሥራ ባሻገር ለተቋሙ ሥራ ትልቅ አቅም የሚፈጥርላቸው ከመሆኑም በተጨማሪ በቀጣይ ከስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት በማኅበሩ ስራና በየስራ ክፍላቸው በመተግበር ተቋማችን ውስጥ በአመራር ላይ የራሳቸውን ጥረት እንደሚጨምሩ ገልጸዋል፡፡
በመዝጊያው ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የማህበሩ ሊቀ መንበር አቶ ካሳሁን ሰቦቃ ከሰልጣኖች ለተነሱ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ የሰጡ ሲሆን የሰው ኃይል ዲቪዥን ለሠራተኞቹ የሚያዘጋጃቸው ስልጠናዎች የተቋሙን ሠራተኞች ብቃት ከፍ የሚያደርግ መሆኑን በማውሳት ለዚህ ስልጠና መሳካት ከፍተኛውን ድጋፍ ላደረጉት የሰው ኃይል ዋና ክፍልና ለኦርጋናይዜሽናል ዴቨሎፕመንት መምሪያ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡