Under Construction

This will close in 20 seconds

55+ ዓመት

የማህበሩ ታሪክ

የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ሠራተኞች ማኅበር መጀመሪያ ጥር 8 ቀን 1958 ዓ.ም ተመሠረተ፡፡ እንዲሁም መጋቢት 17 ቀን 1968 ዓ.ም. እንደገና ተደራጅቶ እና ተጠናክሮ ተመስርቷል፡፡ ማህበሩ የሰራተኛውን የስራ ዋስትና እና ደህንነት ለማስጠበቅ፤ የሰራተኛው ምርታማነት በማሳደግ ከተቋሙ የተሻለ የጥቅም ተጋሪ የሚሆንበትን አቅጣጫ ከማኔጅመንት ጋር በመነጋገር ማስቀመጥ፤ የተቋሙን ራዕይ ፤ ተልዕኮና ዓላማን ለማሳካት ከማኔጅመንት እንዲሁም ከሰራተኛው ጋር በየጊዜው በመመካከር የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ የራሱን አስተዋፅኦ ማድረግ፤ የሰራተኛውን ጥቅማጥቅም ለማስከበርና ከቀደመው የተሻለ መብትና ጥቅም ለማስገኘት በየጊዜው በሁለትዮሽ ላይ የተመሰረተ የህብረት ስምምነት ከማኔጅመንት ጋር በመደራደር እንዲሁም በትክክል ለመፈጸሙ በየደረጃው ክትትል በማድረግ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፍላጎታቸው የተሟላ ሰራተኞች እንዲኖሩ ማስቻል፤ እና ሌሎችንም አላማዎች ለማሳካት ይህ ማህበር ተመስርቷል፡፡

ይህ አንጋፋና ነባር ማህበር በ2003 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን በአዋጅ ሲፈርስ ማህበሩም ትልቅ ችግር ውስጥ ወድቆ የነበረ ሲሆን በወቅቱ ብዙ ሰራተኞች ከስራ ቅነሳ ጋር በተያያዘ ችግር ላይ እንዳይወድቁ አስፈላጊውን ህጋዊ ድጋፍ አድርጓል፡፡ በመቀጠልም አዲስ በተቋቋመው ኢትዮ ቴሌኮም ውስጥ ማህበሩ እንደ አዲስ ቀሪ አባላትን በመያዝና አዳዲስ አባላትን በመጨመር በ4000 አባላት እንደገና ተቋቋመ፡፡ በሂደትም ከዚያ ቀደም ከነበሩት የህብረት ስምምነቶች በሙሉ የተሻለ የህብረት ስምምነት ከማኔጅመንቱ ጋር በማድረግ ለሰራተኛው ጥቅማጥቅም፤ መብትና ደህንነት መቆሙን በማረጋገጡና የስራ ዋስትናውንም በተገቢው መንገድ በማስጠበቁ አዳዲስ አባላት በየጊዜው እንዲቀላቀሉ እና ሙሉ እምነት በማህበራቸው ላይ እንዲኖራቸው አስችሏል ፡፡ በዚሁ መሰረት አሁን ላይ ከአስራ ሁለት ሺ በላይ አባላት በማህበራችን በመታቀፍ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ከማህበራቸው በማግኘት ላይ ይገኛሉ፡፡

ራዕይ

መብትና ጥቅሙ የተከበረለት ሀላፊነቱን በአግባቡ የሚወጣና በስራው የረካ ሰራተኛ መፍጠር፡፡

ተልዕኮ

የማህበሩ አባላትን መብት፤ ጥቅምና ደህንነት በማስከበር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎታቸው እንዲሟላ ምርታማነታቸው እንዲጎለብትና ሰራተኞች ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ የድርጅታችንን ተልዕኮ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሳካ በማገዝ በሀገሪቱ ግንባር ቀደም ማህበር መሆን ነው፡፡

እሴቶች

ባለድርሻ አካላት

የማህበሩ አወቃቀር

የኢትዮ ቴሌኮም መሰረታዊ ሠራተኞች ማኀበር የኢትዮ ቴሌኮም አደረጀጀትን ተከትለው፤ በሪጅኖች፣ በዞኖች፣ በዋናው መ/ቤት፣ በለገሀር /ከስተመር ሰርቪስ/ ፣ አይ.ኤስ.፣ ኦ.ኤንድ ኤም. ፣ በኔትዎርክ ዋና ክፍል፣ በሶርሲንግ እና ፋሲሊቲ ዋና ክፍል እና በዘርፍ ስር የሚደራጁ የዘርፍ ዘርፍ ማኀበራት ይሆናሉ፡፡

Org structure

አበይት ኮሚቴ

የዲሲፕሊን ኮሚቴ

በህብረት ስምምነቱ የተደነገጉትን የዲሲፕሊን ጥሰትን የፈፀመ ሰራተኛ በመመሪያዉ መሰረት አስተማሪ የሆነ የዲስፕሊን እርምጃ  መወሰዱን የሚከታተልና ሰራተኞች ከዲሲፕሊን ግድፈት እራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ የተለያዩ ሃሳቦችን በማቅረብ የማስተማር ስራ የሚሰራ ኮሚቴ ነዉ፡፡

የክበብና መዝናኛ ኮሚቴ

ሰራተኛዉ  ስራዉን በተሳለጠ መልኩ እንዲያከናዉን በሚሰራበት አቅሪቢያ የእረፍት ጊዜዉን በአግባቡ ተጠቅም ወደ ስራዉ እንዲመለስ  የክበብ አገልግሎት መኖሩን ከሌለም እንዲቃቋም ከድርጅቱ ማናጅመት ጋር በመሆን በመመሪያዉ መሰረት እንዲፈጸም የሚያደርግ ኮሚቴ  ነዉ ፡፡

የእድገትና ዝውውር ኮሜቴ

በህብረት ስምምነት መሰረት በተቋሙ ውስጥ ሰራተኞች በሚሳተፉባቸው እድገትና ዝውውር ስራዎች ላይ ተሳታፊ በመሆን በተቀመጠው መስፈርት መሰራቱን የሚያረጋግጥ ኮሜቴ ነው፡፡(ረቂቅ)  

የትምህርትና ስልጠና ኮሜቴ

በየደረጃዉ ያሉ የማህበር የአመራር አካላት በማህበር ቆይታቸዉ የማህበሩን ስራ በሚሰሩበት ጊዜ በእዉቀት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት ለማህበሩ አባላት እንዲሰጡ ያስችላቸዉ ዘንድ የአመራር ክህሎታቸዉን ለማዳበር ከባለ ድርሻ አካለት ጋር በመሆን ስልጠና የሚያዘጋጅ ኮሚቴ ነዉ፡፡

እውቅናዎች

የማህበሩ አመራሮች

Under Construction

This will close in 20 seconds