የኢትዮ ቴሌኮም መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሚያደርገውን አመታዊ ድጋፍ አስቀጠለ
ማህበሩ በየዓመቱ ከሚያደርጋቸው የበጎ አድራጎት ተግባሮች ውስጥ አንዱ የሆነው ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በየዓመቱ የሚያደርገው የ 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ድጋፍ የማህበሩ የክብር አምባሳደርና የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ለሁለተኛ ጊዜ አድርጓል፡፡ በዚህ ወቅት የማህበሩ የስራ ኃላፊዎች ከሰራተኛ ማህበሩ ስራ አስፈጻሚዎች ጋር በአካሄዱት ውይይት የተቸገሩ ወገኖችን በዘላቂነት ለመደገፍ እንዲቻል የማህበሩ ድጋፍ