Under Construction

This will close in 20 seconds

በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አቅመ ደካሞችን እና ታማሚዎችን በመያዝ እንክብካቤ በማድረግ ላይ ለሚገኙ እንዲሁም ተጥለው የሚገኙ ጨቅላ ህፃናትን በማንሳት በማሳደግ ላይ ላሉት እና ድጋፍ በእጅጉ ለሚፈልጉ ስድስት ማህበራት በአጠቃላይ የ300 መቶ ሺ ብር ድጋፍ ሲያደርግ በተመሳሳይ በሪጅን ላሉ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተረጂዎች እና በኮቪድ-19 ምክንያት ለችግር የተዳረጉ ወገኖቻችንን የ300 መቶ ሺ ብር የገንዘብና የአይነት ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡ በዚሁ የድጋፍ ስነስርዓት ላይ የማህበሩ አመራሮች በመገኘት ታማሚዎችን እና አቅም ደካሞችን በማበረታት ድጋፉን ያስረከቡ ሲሆን በዚሁ ወቅት አመራሮቹ በአስተላለፉት መልዕክት እነዚህን ማህበራት በማቋቋም አቅመ ደካሞችንና ህመምተኞችን ደጋፊ ሳይኖራቸው ከመንገድ ላይ በማንሳት ይህንን አይነት ፍፁም ለፈጣሪ መሰጠትን የሚጠይቅ ስብእና በመላበስ ለሚያደርጉት እንክብካቤ ሁሉ ያላቸውን አድናቆት እና ክብር በመግለጽ በቀጣይ በሰራተኞቻችንም ሆነ በማህበራችን ይህንን አይነት ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ አፅንኦት በመስጠት ገልፀዋል፡፡ በተረጂዎቹ በኩልም ተቋማችንም ሆነ ሰራተኞቻችን በተለያየ መንገድ ለሚያደርጉላቸው ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና በማቅረብ ድጋፉ ቀጣይነት እንዲኖረው ጠይቀዋል፡፡ በተመሳሳይ በሁሉም ሪጅኖቻችን እና ዞኖች ከእናት ማህበሩ ከተመደበው አነስተኛ ገንዘብ ባሻገር ከራሳቸውም በሚደረግ መዋጮ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች በተደጋጋሚ በመድረስ አለኝታነታቸውን አስመስክረዋል፡፡ ለዚህም ማህበራችን ለሰራተኞቹ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

Post a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Under Construction

This will close in 20 seconds